Yene Mastawesha

Yene Mastawesha

ትንፋሼ ተቀርፃ ይቀመጥ ማልቀሻ
ይሄ ነው የሞቱክኝ ለት የኔ ማስታወሻ
ትንፋሼ ተቀርፃ ይቀመጥ ማልቀሻ
ይሄ ነው የሞቱክኝ ለት የኔ ማስታወሻ
ውበቷን ሣሞግስ የለምለም አገሬን
ማንም አይዘነጋ በጩኸት መኖሬን
ዜማ እንጉርጉሮዬ የግሌን ቅላፄ
ተቀርፆ ይቀመጥ ታሪኬ ነው ጽምፄ
ጽምፃዊ ዘፋኝ ነኝ አንጎራጉራለው
ይኸው ነው ታሪኬ ሌላ ምን አውቃለው
ይቀመጥ ትንፋሼ ለቀሪው ወዳጄ
ስጡት ትዝ ብለው ሰላም ያለ ልጄ
ትንፋሼ ተቀርፃ ይቀመጥ ማልቀሻ
ይሄ ነው የሞቱክኝ ለት የኔ ማስታወሻ
ያስቀየምኩት ቢኖር የጠላኝ በቁሜ
ድምፄን ሰምቶ ያፅናኝ ለረገፈው አፅሜ
እኔን ለበደሉኝ ይቅር ብያለው ቂሜን
በኔ የከፋችው ይቅር በሉት አፅሜን
ለቅርብ ወዳጄ ለሚወደኝማ
አይገደውም እምባ ትንፋሼን ሲሰማ
ለቅርብ ወዳጄ ለሚወደኝማ
አይገደውም እምባ ትንፋሼን ሲሰማ
ለቅርብ ወዳጄ ለሚወደኝማ
አይገደውም እምባ ትንፋሼን ሲሰማ

Песен-НИКИ

Загрузка...

Похожие песни